የአባልነት መስፈርት፣ ግዴታዎችና መብቶች

የአባልነት መስፈርት፣ ግዴታዎችና መብቶች

የአባልነት ግዴታ

 • በማኅበሩ የስራ አስፈጻሚ ወይንም በማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን ማክበር፣
 • የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ ማክበር፣
 • ሕጋዊ መሠረትን ተከትለው ከማኅበሩ የሚተላለፉ ትእዛዛትን መቀበልና መፈፀም፣ በማኅበሩ ውስጥ በኮሚቴ አባልነት ሲካተቱ እንዲሁም በራስ ተነሳሽነት ማገልገል፣
 • የአባልነት ክፍያዎችን ወቅቱን ጠብቆ መክፈል፣
 • አድራሻን ፣ ወቅታዊ የሙያ ደረጃንና የሥራ አድራሻን ለማኅበሩ ማሳወቅ፣
 • የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ፣ የአባልነትን መብትና ግዴታዎች ማዎቅና መቀበል፣

የአባልነት ክፍያዎች

 • ማንኛውም አባል የአባልነት ክፍያዎችን ወይንም መዋጮዎችን በወቅቱ መክፈል አለበት፡፡
 • የየዓመቱ ወርሃዊ የአባልነት ክፍያ እስከዓመቱ መጨረሻ (የማኅበሩ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ እስከሚካሄድበት ቀን) ድረስ ተከፍሎ መጠናቀቅ አለበት፡፡
 • ያለበትን ዓመት ወርሃዊ የአባልነት ክፍያ ያጠናቀቀ አባል የቀጣዩን አንድ ወይም ከዚያ በላይ ዓመታት የአባልነት ክፍያ ቅድሚያ ከከፈለ ፣ ቅድሚያ ከከፈለው ላይ የአስር በመቶ (10%) ቅናሽ ይደረግለታል፡፡
 • ተቋማዊ አባላት ለመረጡት የአባልነት ደረጃ በሚከተለው ሠንጠረዥ መሠረት ይከፍላሉ፡፡

የአባልነት ጥያቄ አቀራረብና ምዝገባ

 • ማንኛውም የማኅበሩ አባል ለመሆን የሚፈልግ ሰው ወይንም ድርጅት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ቅጽ መሠረት ማመልከቻውን በአቅራቢያው ለሚገኝ የማኅበሩ ቅርንጫፍ ወይንም ለማኅበሩ ዋና ጽ/ቤት ያቀርባል፣
 • ማመልከቻው የቀረበው ለማኅበሩ ቅርንጫፍ ከሆነ የቅርንጫፉ ስራ አሰኪያጁ የጥያቄውን አግባብነት ከመረመረ በኋላ ተገቢ ሆኖ ሲያገኘው አመልካቹን በአባልነት ይመዘግባል፡፡
 • የክብር አባል እጩ በማእከላዊው ሥራ አስፈጻሚ አቅራቢነት በጠቅላላ ጉባዔው ተቀባይነት ሲያገኝ የክብር አባል ሆኖ ይመዘገባል፡፡
 • ለመደበኛ አባል ፣ ተባባሪ አባል አእና የተማሪ አባል የመታወቂያ ካርድ እነዲሁም የደረት ባጅ ከማኅበሩ ይሰጣቸዋል፡፡ ለልዩ አባል ፣ የእድሜ ልክ አባል እና የክብር አባል ከመታወቂያ ካርድ በተጨማሪ የአባልነት የምስክር ወረቀት ከማኅበሩ ይሰጣቸዋል፡፡ ለተቋማዊ አባላት ደግሞ የአባልነት የምስክር ወረቀት ከማኅበሩ ይሰጣቸዋል፡፡

አባልነት የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች

ከአባልነት ስለመታገድ

 • የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አንድን አባል በቂ በሆነ ምክንያት ማገድ ይችላል፡፡ ስለ ሁኔታውም ለጠቅላላ ጉባዔ አቅርቦ እገዳው እንዲቀጥል ወይም እንዲነሳ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
 • አንድ አባል የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከአባልነት ሲታገድ የታገደበት ምክንያት ተገልጾ ይጻፍለታል፡፡ ለዚህም መልስ የመስጠት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚደርሰው እገዳ ጊዜያዊ ሲሆን ውሳኔው ቋሚ የሚሆነው በጠቅላላ ጉባዔ ሲፀድቅ ብቻ ነው፡፡
 • ለተከታታይ ሁለት ዓመታት የአባልነት ክፍያ ያልከፈለ አባል ማስጠንቀቂያ ይጻፍለታል፡፡
 • በማኅበሩ ውሳኔ የታገደ አባል ሁኔታው የተሻሻለ መሆኑን ጠቅላላ ጉባዔው ካመነበት እገዳውን በማንሳት እንደገና በአባልነት ሊቀበለው ይችላል፡፡
 • አንድ አባል ቢበዛ ለአንድ ዓመት ከታገደ በኋላ የእገዳው ምክንያት ተመርምሮ እንደገና በአባልነት እንዲቀጥል ወይም ከአባልነት ሙሉ በሙሉ እንዲሰናበት ይደረጋል እንጅ ከአንድ ዓመት በላይ በእገዳ ሊቆይ አይገባም፡፡

ከአባልነት ስለመሠናበት

 • ማንኛውም አባል ከሁለት ዓመት በላይ የአባልነት ክፍያውን ያለ በቂ ምክንያት በማቋረጡ ከታገደ በኋላ ማሳሰቢያዎች ደርሰውት ለመክፈል ፈቃደኛ ሳይሆን ሲቀር ከአባልነት ይሠናበታል፡፡
 • ማንኛውም አባል የሙያ ሥነ-ምግባርን የሚያጎድፍ ተግባሮችን የፈጸመ ወይም ሙያውን በተመለከተ ወንጀል ፈጽሞ በፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠው እንደሆነ ከአባልነት ይሠናበታል፡፡ የፍርድ ቤት እገዳው ከተጠናቀቀ በኋላ ግን እንደአዲስ አባል መመዝገብ ይችላል፡፡
 • ከማኅበሩ የተሠናበተ አባል ቀደም ብሎ የከፈለው ገንዘብ ተመላሽ አይሆንለትም፡፡ ከማኅበሩ የሚፈለግበት እዳ ካለም የማጠናቀቅ ግዴታ ይኖርበታል፡፡

አባላት ራሳቸውን ከአባልነት ስለሚያገሉበት

 • ማንኛውም አባል በራሱ ፈቃድና ውሳኔ ከማኅበሩ አባልነት ራሱን ሊያገል ይችላል፣ ይህንንም ለማእከላዊው ሥራ አስፈጻሚ በቅድሚያ በጽሁፍ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
 • ማንኛውም አባል ከሶስት ዓመት በላይ የአባልነት ክፍያውን ያለ በቂ ምክንያት ሲያቋርጥ ራሱን ከአባልነት እንዳገለለ ይቆጠራል፡፡
 • ማኅበሩን በፈቃዱ የለቀቀ ማንኛውም አባል ቀደም ብሎ የከፈለው መዋጮ አይመለስለትም፡፡ ከማኅበሩ የሚፈለግበት እዳ ካለም ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
 • በፍቃዱ የወጣ Aባል እንደገና አባል ለመሆን ጥያቄ አቅርቦ ከተፈቀደለት እንደ አዲስ (ጀማሪ) አባል ይመዘገባል፡፡ አሳማኝና በቂ ምክንያት ካልቀረበ በስተቀር በዚህ ዓይነት ሁኔታ እንደገና መመዘገብ የሚቻለው ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡

የእድሜ ልክ አባላት

Prerequisites
 • የመደበኛ አባልነት መሥፈርትን የሚያሟላና የስራ አስፈጻሚ በሚወሰነው መሠረት የረዥም ጊዜ የአባልነት ክፍያ በአንድ ጊዜ የከፈለ ግለሰብ የእድሜ ልክ አባል ይሆናል፡፡ የእድሜ ልክ Aባላት በሥራ አስፈፃሚ የተወሰነውን የረዥም ጊዜ ክፍያ ከከፈሉ በኋላ ከዓመታዊ የአባልነት ክፍያ ነጻ ይሆናሉ
 
Benefits
 • የመደበኛ አባላት የሚያገኟቸውን ጥቅማ ጥቅሞች በሙሉ ያገኛሉ
 
Requirements
 
Registration fee
 
Membership fee
 

ልዩ አባላት

Prerequisites
 • በስነ-ምግባሩ አርአያ የሆነና የስራ አስፈጻሚ የሚወሰነውን ክፍያ በአንድ ጊዜ የከፈለ ግለሰብ ወይንም ድርጅት ልዩ አባል ሆኖ ይመዘገባል፡፡ የስነ-ምግባር ጉድለት ያለበት ልዩ አባል ከአባልነቱ ይሰረዛል
 
Benefits
 • የመደበኛ አባልነትን መሥፈርት የሚያሟሉ ልዩ አባላት በማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ እና ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ውስጥ የሚያገለግሉ አባላትን የመምረጥ እና/ወይንም ራሳቸው የመመረጥ መብት አላቸው
 • የመደበኛ አባልነትን መሥፈርት የማያሟሉ ልዩ አባላት በማኅበሩ ውስጥ በሚደረጉ ምርጫዎች የመምረጥና የመመረጥ እንዲሁም በማኅበሩ አሠራር ውስጥ ድምፅ በሚሰጥባቸው ውሳኔዎች ድምፅ የመስጠት መብት የላቸውም
 • ልዩ አባልነታቸውን የሚገልጥ የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል
 • ከላይ የተገለጠው እንደተጠበቀ ሆኖ የመደበኛ አባልነትን መሥፈርት የማያሟሉ ልዩ አባላት መደበኛ አባላት የሚያገኟቸውን ጥቅማ ጥቅሞች ያገኛሉ
 
Requirements
 
Registration fee
 
Membership fee
 

የክብር አባላት

Prerequisites
 • ለፋርማሲ ሙያ እድገትና ሕብረተሰቡ ከሙያው ተጠቃሚ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱ የተረጋገጠለት ግለሰብ የስራ አስፈጻሚ አቅራቢነት በጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔ የክብር አባል መሆን ይችላል፡፡ የክብር አባልነት አሰጣጥ መመሪያ/ሥርዓት/ ይዘጋጅለታል
 
Benefits
 • ማኅበሩ በሚያዘጋጀው ዓመታዊ ሳይንሳዊ ጉባኤ ልዩ ቦታ ተዘጋጅቶላቸው ጉባዔውን እንዲከታተሉ ይደረጋል
 • የክብር አባልነታቸውን የሚገልጥ የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል
 • ከመምረጥና መመረጥ ፣ እንዲሁም በማኅበሩ አሠራር ውስጥ ድምፅ በሚሰጥባቸው ውሳኔዎች ድምፅ ከመስጠት በስተቀር መደበኛ አባላት የሚያገኟቸውን ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ያገኛሉ፡፡ የመደበኛ አባልነት መስፈርትን የሚያሟሉ ከሆነ ግን የመምረጥ፣ የመመረጥና ድምጽ የመስጠት መብት ይኖራቸዋል
 
Requirements
 
Registration fee
 
Membership fee
 

የተማሪ አባላት

Prerequisites
 • በፋርማሲ ዘርፍ በዲግሪ መርሃ ግብር ከታወቀ የትምህርት ተቋም ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ፣ቢያንስ ከ3ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ ትምህርት የደረሱና በዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተማሪዎች
 • ተማሪ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሚማሩበት ተቋም ኃላፊ ማቅረብ የሚችሉ
 • ማንኛውም የተማሪ አባል ትምህርቱን እንደአጠናቀቀ ከሚመለከተው ሕጋዊ አካል የሙያ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያገኘ የመደበኛ አባላት የሚከፍሉትን ክፍያ በመክፈል ከተማሪ አባልነት ተሰርዞ በመደበኛ አባልነት ይመዘገባል
 • በፋርማሲ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸውና የሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) ወይንም ከዚያ በላይ የሆነ ትምህርት በመከታተል ላይ ያሉ ተማሪዎች በተማሪ አባልነት መመዝገብ አይችሉም
 • የተማሪ አባላት በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን አቋረጠው ከትምህርት ቤት ከተሰናበቱ የተማሪነት አባልነታችው ይሠረዛል
 
Benefits
 • ለቅርንጫፍና የዘርፍ ማስተባበሪያ ኮሚቴ አባላትን የመጠቆምና የመምረጥ አንዲሁም የመመረጥ መብት ኣላቸው
 • ከቅርንጫፍና የዘርፍ ክትትል ኮሚቴ በስተቀር በማኅበሩ ውስጥ በሚደረጉ ሌሎች ምርጫዎች የመመረጥና የመምረጥ መብት አይኖራቸውም
 • በዚህ አንቀጽ ን/አንቀጽ 5/ለ/ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ የመደበኛ አባላት የሚያገኙትን ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ያገኛሉ
 
Requirements
 
Registration fee
 
Membership fee
 

ተባባሪ አባላት

Prerequisites
 • ከሚመለከተው ሕጋዊ አካል እውቅና ካገኘ የትምህርት ተቋም በፋርማሲ ሙያ በዲፕሎማና ከዚያ በታች የተመረቀ ወይንም በሌላ ሙያ የመጀመሪያ ዲግሪ/ዲፕሎማ ኖሮት በፋርማሲ የማስተርስ ዲግሪ ወይም ፒ.ኤች.ዲ ያለው
 • ከሚመለከተው ሕጋዊ አካል የሙያ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያገኘ እና ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው
 • በዜግነት ኢትዮጵያዊ ባይሆንም ከታወቀ የትምህርት ተቋም በየትኛውም ደረጃ በፋርማሲ የተመረቀና ከሚመለከተው ሕጋዊ አካል በኢትዮጵያ በሙያው ለመሠማራት የሙያ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያገኘ
 • በሌሎች የጤና ሙያዎች ከታወቀ የትምህርት ተቋም ተመርቆ ከሚመለከተው ሕጋዊ አካል የሙያ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያገኘ
 • በማህበራዊም ሆነ በተሰጥሮ ሳይንስ ሙያዎች ከታወቀ የትምህርት ተቋም ቢያንስ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቆ ለፋርማሲ ሙያ እድገት ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
 • ከሚመለከተው መንግስታዊ አካል ፈቃድ የተሰጠው የባህል መድኃኒትና ሕክምና አዋቂ
 
Benefits
 • ማኅበሩ በሚያካሂዳቸው ሳይንሳዊ ኮንፈረንሶችና ሴሚናሮች የመሳተፍ መብት Aላቸው
 • የኢትዮጵያን ፋርማሲዩቲካል ጆርናል፣ ፋርማ-ፎረም እና ሌሎች የማኅበሩ ኅትመቶችን በነጻ ወይንም በልዩ ሁኔታ ለአባላት ተብሎ በተወሰነ አነስተኛ ክፍያ ያገኛሉ
 • ከላይ የተገለጠው እንደተጠበቀ ሆኖ ተባባሪ አባላት በማኅበሩ የስራ አስፈጻሚ እና ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ውስጥ የሚያገለግሉ አባላትን የመምረጥ እና ራሳቸውም የመመረጥ መብት የላቸውም፡፡ እንዲሁም በማኅበሩ አሠራር ውስጥ ድምፅ በሚሰጥባቸው ውሳኔዎች ድምፅ የመስጠት መብት የላቸውም
 
Requirements
 
Registration fee
 
Membership fee
 

ተቋማዊ አባላት

Prerequisites
 • ማንኛውም በኢትዮጵያ ውስጥ በፋርማሲ ዘርፍ ወይንም በሌላ የጤና ዘርፍና ተያያዥ ሥራ ላይ የተሰማራ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት የማኅበሩ ተቋማዊ አባል መሆን ይችላል
 • በአንቀጽ 12 መሠረት ተቋማዊ አባላት መደበኛ ተቋማዊ አባላት እና ልዩ ተቋማዊ አባላት ተብለው ይከፈላሉ
 
Benefits
 • ማንኛውም የማኅበሩ መደበኛ ተቋማዊ አባል በተቋሙ ዋና ሥራ አስኪያጅ/ዳይሬክተር ተወካይነት ወይም አንድ ሌላ ተወካይ ማኅበሩ በግብዣ በሚያካሂዳቸው ሣይንሳዊ ኮንፈረንሶች፣ ሴሚናሮች መሣተፍ ይችላል
 • መደበኛ ተቋማዊ አባላት ከመደበኛ (ቋሚ) ኮሚቴዎች ሌሎች ማኅበሩ በሚያቋቁማቸው ሌሎች ኮሚቴዎች የመሣተፍ መብት አላቸው
 • መደበኛ ተቋማዊ አባላት ማኅበሩ የሚሠጣቸውን እንደ የሕትመት፣ ቤተ መጻሕፍት፣ ክበብ የመሳሰሉ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የመጠቀም መብት አላቸው፡፡ አገልግሎቱ የሚሰጠው የተቋሙ ሥራ አስኪያጅ ወይንም የተቋሙ ሥራ አስኪያጅ ለሚወክለው አንድ የተቋሙ ሠራተኛ ነው
 • መደበኛ ተቋማዊ አባላት ማኅበሩ በሚያወጣቸው ሕትመቶች (የፋርማ-ፎረም፣ ቡክ ኦፍ አብስታራክት፣ የዓመታዊ ሣይንሳዊ ጉባዔ የጥሪ ፖስተር) ላይ የስም ዝርዝራቸው እና/ወይንም አርማቸው ይወጣል
 • መደበኛ ተቋማዊ አባላት ማኅበሩ በሚያወጣቸው ሕትመቶች ላይ የድርጅታቸውን ሥራ ወይም ምርት ለማስተዋወቅ የ30% ዋጋ ቅናሽ ይደረግላቸዋል
 • መደበኛ ተቋማዊ አባላት ማኅበሩ በሚያዘጋጃቸው ሙያዊ ሥልጠናዎች በድርጅታቸው ያሉ ተቀጣሪ ባለሙያዎችን ለማሠልጠን የ20% ዋጋ ቅናሽ ይደረግላቸዋል
 • መደበኛ ተቋማዊ አባላት ፋርማ-ፎረምና የማኅበሩን ሳይንሳዊ መጽሔት ከእያንዳንዱ እትም በነፃ ያገኛሉ
 • ድምጽ የመስጠት መብት የላቸውም
 
Requirements
 
Registration fee
 
Membership fee
 

መደበኛ አባላት

Prerequisites
 • ከሚመለከተው ሕጋዊ አካል እውቅና ካገኘ የትምህርት ተቋም በፋርማሲ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ያለው
 • ከሚመለከተው ሕጋዊ አካል የሙያ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የተሰጠው
 • ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው
 • ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያሟላ ከሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ ኗሪ ቢሆንም መደበኛ አባል መሆን ይችላል
 
Benefits
 • ማኅበሩ በሚያካሂዳቸው ጠቅላላ ጉባዔዎች ፣ ሳይንሳዊ ኮንፈረንሶችና ሴሚናሮች መሳተፍ ይችላሉ
 • በማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ እና ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ውስጥ የሚያገለግሉ አባላትን የመምረጥ እና/ወይንም የመመረጥ እንዲሁም በማኅበሩ አሠራር ውስጥ ድምፅ በሚሰጥባቸው ውሳኔዎች ድምፅ የመስጠት መብት አላቸው
 • አትዮጵያን ፋርማሲዩቲካል ጆርናል ፣ ፋርማ-ፎረም እና ሌሎች የማኅበሩ ኅትመቶችን በነጻ ወይንም በልዩ ሁኔታ ለአባላት ተብሎ በተወሰነ አነስተኛ ክፍያ ያገኛሉ
 • የማኅበሩ አባላት መሆናቸውን በጽሑፍ መግለጥ ይችላሉ
 • ማኅበሩ ለአባላቱ የሚሰጣቸውን ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በሙሉ የማግኘት መብት አላቸው
 
Requirements
 
Registration fee
 • One time fee100
 
Membership fee
 • 200 per annum